መሀንዲስነት

Article on other languages:

ምህንድስና ማለት የሳይንስ እና የሂሳብ መርሆችን በመከተል እንዲሁም የማስተዋል እና የምርምር ችሎታን በመጠቀም በተመጣጣኝ ወጪ ለሰው ልጆች ጥቅም ሊውሉ የሚችሉ ግንባታዎችን መቀየስ፣ ተቋማትን መስራት፣ የመገልገያ ቁሳቁሶችን መፍጠር እና ይተለያዪ የቴክኒክ ችግሮችን መፍትሔ ማግኘትን ያጠቃልላል። ይህንን አይነት ስራ የሚሰራ ሰው 'መሐንዲስ' ተብሎ ይጠራል። የምህንድስና ስራ የተለያዩ ዘርፎች ያሉት ሲሆን በተለምዶ ከሚታወቁት ዘርፎች ውስጥ ሲቭል፣ መካኒካል፣ ኤሌክትሪካል እና ኬሚካል ይጠቀሳሉ። የተክኖሎጂ ማደግ ተከትሎ በአሁኑ ወቅት የምህንድሲና ዘርፎች ሰፋ ያሉ ናቸው። አዲሶቹ የምህንድስና የትኩረት ዘርፎች ሁሉን አቀፍ (መልታይ ዲሲፕለናሪ) እና ውሱን በሆነ የተግባር አቅጣጫ (ስፐሲፊክ አፕልኬሽን) ላይ የተመሰረቱ ናቸው።

This article is from Wikipedia. All text is available under the terms of the GNU Free Documentation License.